Family Communication
ከቤተሰቦች ጋር እንዴት እንደምንገናኝ
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ወቅታዊ እና ጠቃሚ ግንኙነት ከቤተሰብ ጋር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ያውቃል።እነዚህ መሳሪያዎች የዲስትሪክቱ ኦፊሴላዊ የመገናኛ ዘዴዎች ናቸው።
የመገናኛ መሳሪያዎች
የስልክ መልዕክቶች: በትምህርት ቀን ወይም በማለዳ የሚደረጉ ጥሪዎች እንደ የትምህርት ቤት መዘጋት ወይም መዘግየት ያሉ ድንገተኛ ሁኔታዎች ወይም አስፈላጊ መረጃዎች የሚተላለፉበት ናቸው።በየከሰአት በኋላ ጥሪዎች አጠቃላይ መረጃ፣አስታዋሾች እና የተማሪ አቴንዳንስ ማሳወቂያዎች ይጋራሉ።
የጽሑፍ መልዕክቶች: ድስትሪክቱ የጽሑፍ መልእክት ለቤተሰቦች ለመላክ Talking Points ይጠቀማል። ትምህርት ቤቶች እና አስተማሪዎች Talking Points መጠቀም ይችላሉ።ቤተሰቦች የጽሑፍ መልእክት ከመቀበል በተጨማሪ የTalking Points app መጠቀም ይችላሉ—ከ Apple App Store እና ከ Google Play ማውረድ ይችላሉ።
የኢሜል መልዕክቶች: ዲስትሪክቱ ደብዳቤዎች፣የፕሮግራም ማሻሻያዎች፣ የማህበረሰብ በራሪ ወረቀቶች እና ጋዜጣዎች ለመላክ ኢሜል ይጠቀማል።
የዲስትሪክት እና የትምህርት ቤት ድረ–ገጾች: ዲስትሪክቱ እና ትምህርት ቤቶች የዜና ማስታወቂያዎች፣ የቀን መቁጠሪያዎች እና የመገናኛ መረጃዎች ያትማሉ።ድንገተኛ ሁኔታ ሲከሰት፣በየሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ድረ-ገጾች ላይ የሚሰጠውን ማስጠንቀቅያ ይመልክቱ።የድረ-ገጽ ጎብኚዎች በPeachjar በኩል የሚጋሩ የማህበረሰብ በራሪ ወረቀቶችን በእያንዳንዱ የትምህርት ቤት ድህረ ገጽ ግርጌ ባለው ሊንክ ማየት ይችላሉ።
የቤተሰብ ፖርታል: The Source የተማሪ አቴንዳንስ፣የትምህርት ቤት ክፍያዎችን የሚከፈልበት አገናኝ እና የተማሪ የእድገት ሪፖርቶችን ጨምሮ የተለያዩ መረጃዎች አለው።
ማህበራዊ ሚዲያ: ጠቃሚ ማስታወቂያዎች፣ስለ ተማሪዎቻችን፣ሰራተኞቻችን እና ትምህርት ቤቶቻችን ታሪኮች እና ሌሎች ለማግኘት በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከተሉን።
Facebook @seattlepublicschools
Instagram @seattlepublicschools
Twitter @seapubschools
ቤተሰቦች መረጃ እንዲኖራቸው ምን ማድረግ አለባቸው
እባክዎን ከትምህርት ቤቶች ወይም ከድስትሪክቱ ለመገናኘት የመገናኛ መረጃዎን ያዘምኑ።
የመገናኛ መረጃዎን እንዴት እንደሚያዘምኑ
መልዕክቶችዎን ያስተዳድሩ፡ለአንዳንድ መልዕክቶች የስልክ ጥሪዎች ለሌሎች ደግሞ ኢሜይል ይፈልጋሉ ?
ምርጫዎችዎን በመስመር ላይ ያስተካክሉ ።go.schoolmessenger.com. ይጎብኙ።በልጅዎ ትምህርት ቤት ፋይል ላይ ባለው ኢሜይል ይግቡ እና እርስዎን እንዴት እንደምናገኝዎት ያዘምኑ።
ኢሜል እና ስልክ ቁጥሮችን ያዘምኑ: ትምህርት ቤትዎ ወቅታዊ የመገናኛ መረጃ እንዳለው ያረጋግጡ።
በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ወላጆች እና አሳዳጊዎች በሶርስ ላይ(The Source) በሚገኘው የተማሪው የማረጋገጫ( Student Verification) ቅጽ አድራሻቸውን ማዘመን ይችላሉ።በዓመቱ ውስጥ ስልክ ቁጥሮች፣ኢሜሎች እና አድራሻ ለማዘመን የትምህርት ቤቱን የፊት ቢሮ ያነጋግሩ።
የአደጋ ጊዜ ግንኙነት
በተማሪዬ ትምህርት ቤት ድንገተኛ አደጋ ካለ እንዴት አውቃለሁ? የተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነት ቅድምያ የመንሰጠው ጉዳይ ነው። ዲስትሪክቱ እና ትምህርት ቤቶች ትክክለኛ እና ወቅታዊ መረጃ ለማጋራት ይጥራሉ።
- ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች አውቶማቲክ የስልክ ጥሪ፣የጽሑፍ መልእክት እና/ወይም ኢሜይል ይደርሳቸዋል።
- በብዙ ሁኔታዎች፣ሁኔታው ካበቃ በኋላ ትምህርት ቤቶች የክትትል መልእክት ይልካሉ።
- እባኮትን ይፋዊ ያልሆኑ መረጃዎችን ከማጋራት ለመዳን ከህዝብ ጉዳዮች ወይም ከእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የሚመጡ ኦፊሴላዊ መልዕክቶችን ይከታተሉ።
ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ የትምህርት ቤት መዘግየቶች ወይም መዘጋት
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የአየር ጠባይ ሁኔታዎችን በቅርበት ይከታተላሉ እንዲሁም በተቻለ ፍጥነት ለተማሪዎች፣ለቤተሰቦች እና ሰራተኞች የትምህርት ቀንን የሚመለከቱ አዳዲስ መረጃዎችን ያሳውቃል።
በአስከፊ የአየር ሁኔታ ምክንያት የመጓጓዣ ለውጦች አንዳንድ ጊዜ የአየር ሁኔታ በዲስትሪክቱ መደበኛ የመጓጓዣ አሠራር ላይ ለውጥን ሊያስገድድ ይችላል።ለበለጠ መረጃ ን ይጎብኙ
መረጃ ይኑርዎት የአየር ጠባይ ሁኔታዎች የጊዜ ሰሌዳ ለውጥ የሚያስከትል ከሆነ፣በሚከተሉት መንገዶች እናሳውቃለን:
- የቴሌቪዥን እና የሬዲዮ ጣቢያዎች
- የአካባቢ ቲቪ: KOMO 4, KING 5, KIRO 7, Q13 FOX
- ሬዲዮ: KOMO AM 1000, KIRO 97.3 FM
- አውቶማቲክ የስልክ ጥሪዎች፣ኢሜይሎች እና የጽሑፍ መልእክቶች
- የዲስትሪክት እና የትምህርት ቤት ድረገጾች