የላቀ ትምህርት የብቁነት ግምገማ ሂደት ዝመና 2022-23
Summary : የተማሪዎን የብቃት ውሳኔ ሓሙስ፣ግንቦት 5 በኢሜል ወይም በፖስታ ይደርሰዎታል።
የላቀ ትምህርት የብቁነት ግምገማ ሂደት ዝመና 2022-23
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች እያንዳንዱ ተማሪ እንዲበለጽግ የሚረዳውን የትምህርት አገልግሎት እንዲያገኝ ለማድረግ ቁርጠኛ ነው።ይህ፣ የላቀ ትምህርት አገልግሎቶች የብቁነት ውሳኔዎች እና የብቁነት መረጃ ለቤተሰቦች የምንጋራበት ጊዜ መለወጥ ይጨምራል።
በዚህ አመት ብቁነትን ለመወሰን ብዙ የመረጃ ምንጮችን ተጠቅመናል።እነዚህም የቤተሰብ/አሳዳጊ የዳሰሳ ጥናት፣የመምህራን ግብአት፣የፈተና ውጤቶች እና ደረጃውን የጠበቁ የክልል የፈተና ውጤቶች ያካትታሉ።
ልጅዎለላቀትምህርትአገልግሎትብቁመሆኑንመቼያውቃሉ
እኛ በአሁኑ ጊዜ ሁሉንም የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የK-8 ክፍል ተማሪዎችን እየገመገምን ነው። ይህ ግምገማ በሚቀጥለው የትምህርት አመት የከፍተኛ አቅም ያላቸው (Highly Capable) እና የላቀ ትምህርት(Advanced Learning) አገልግሎቶች ለማግኘት ብቁ የሆኑትን ይወስናል።
የተማሪዎን የብቃት ውሳኔ ሓሙስ፣ግንቦት 5 በኢሜል ወይም በፖስታ ይደርሰዎታል።
እያንዳንዱተማሪለላቀትምህርትአገልግሎቶችግምትውስጥይግባል
ከፍተኛ አቅም ያላቸው (Highly Capable (HC)):ተማሪዎች ከክፍል ደረጃ በላይ እየሰሩ ከሆነ። እነዚህ ተማሪዎች ሁለት አማራጮች አሏቸው፡
- አሁን ባሉበት ትምህርት ቤት ሆነው በክፍላቸው ውስጥ የላቀ ትምህርት አገልግሎችን ማግኘት ወይም
- በሚቀጥለው ዓመት በ cohort pathway ትምህርት ቤት መጀመር።በcohort pathway ትምህርት ቤት፣ተማሪዎች ከሌሎች HC ተማሪዎች ጋር የተፋጠነ ትምህርት ያገኛሉ (cohort የተማሪዎች ቡድን ነው)።
የላቀ ትምህርት ተማሪ (Advanced Learner (AL)): ተማሪዎች ከክፍል ደረጃ በላይ እየሰሩ ነው። እነዚህ ተማሪዎች አሁን ባሉበት ትምህርት ቤት ተጨማሪ የትምህርት እድሎችን እንደሚፈልጉ ያሳያሉ።
ተከታታይ የላቀ ትምህርት ተማሪ (Continuing Advanced Learner (CAL)): እነዚህ ተማሪዎች ባለፈው አመት የላቀ ትምህርት ተማሪዎች የነበሩ እና በሚቀጥለው አመት በAL ፕሮግራም የሚቀጥሉ ናቸው።
በዚህ የዳታ ግምገማ ብቁ አይደለም(Not Eligible (NE) in this Review: ተማሪዎች በቂ መረጃ አልነበራቸውም ወይም መረጃቸው በዚህ ጊዜ የHC ወይም የAL አገልግሎቶች እንደሚያስፈልጋቸው አላሳየም።
ቤተሰቦች ውሳኔውን እንዴት ይግባኝ ማለት እንደሚችሉ
ቤተሰቦች ውሳኔውን እስከ አርብ፣ግንቦት 20 ድረስ ይግባኝ የማለት እድል አላቸው። እያንዳንዱ ቤተሰብ ይግባኝ ለማቅረብ 10 ቀናት አለው።
የይግባኝ መረጃ በብቃት ደብዳቤዎ ውስጥ ይካተታል። ተጨማሪ መረጃ በ Advanced Learning appeals webpage ላይ ማግኘት ይችላሉ።