በታቀዱት የደወል ጊዜ ለውጦች ዝመናዎች
Summary : እነዚያን ተግዳሮቶች ለመፍታት ብዙ ጊዜ እየወሰድን ነው።
የታቀዱት የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ሰአታት (የደወል ሰአታት)ለውጦች እንደተጠበቀው በሚያዝያ 4 በነበረው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ አልቀረቡም።
ይህ የታቀደው ለውጥ ለቤተሰቦች እና ሰራተኞች ሊፈጥረው ስለሚችል ችግር ከቤተሰቦቻችን እና ከማህበረሰብ አጋሮቻችን ብዙ አስተያየቶችን ተቀብለናል።እነዚያን ተግዳሮቶች ለመፍታት ብዙ ጊዜ እየወሰድን ነው።
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችን በሰዓቱ ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርስ እና ለመማር ዝግጁ የሚያደርግ አስተማማኝ ትራንስፖርት ለማቅረብ ቁርጠኛ ነው።ይህንን እቅድ ስንገመግም፣ሰራተኞች በሚቀጥሉት በርካታ ሳምንታት ከትምህርት ቤቶች፣ቤተሰቦች እና አጋሮች ጋር መስራታቸውን ይቀጥላሉ።እኛም ወቅታዊ መረጃዎችን በተቻለ ፍጥነት ለቤተሰቦች ማሳወቅ እንቀጥላለን።
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎችን ጨምሮ ወቅታዊ መረጃዎችን በየደወል ጊዜ ድረ-ገጽ( bell times webpage)ላይ ማግኘት ይችላሉ።
ስለታቀዱት ለውጦች አስመልክቶ በእንነጋገር አገናኝ(Let’s Talk link )እንዲሁም በሌሎች ዘዴዎች ላገኛሁን ሁሉ እናመሰግናለን።ሁሉንም ግብረመልሶች መገምገማችንን እንቀጥላለን እንዲሁም ከሰራተኞች እና ከትምህርት ቤት ቦርድ ዳይሬክተሮች ጋር እናጋራለን።አስተያየቶችዎን እና ስጋቶችዎን ለማጋራት የተሻለውን መንገድ እንነጋገር(Let’s Talk) ነው።