ለሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች፣ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ያለንን ቁርጠኝነት እንደገና ማረጋገጥ
Summary : ሁሉንም ተማሪዎች ለማስተማር ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ አለብን።እርስዎ ከየትም ቢሆኑም፣ እዚህ ቦታ አልዎት።
ለሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች፣ሰራተኞች እና ቤተሰቦች ያለንን ቁርጠኝነት እንደገና ማረጋገጥ
ውድ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦች እና ሰራተኞች፣
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ዘር፣ሃይማኖት፣ብሔር፣የስደት ሁኔታ፣ፆታዊ ማንነት ወይም የፆታ ዝንባሌ ሳይለይ ለእያንዳንዱ ተማሪ ደህንነቱ የተጠበቀ፣እንግዳ ተቀባይ እና አካታች የትምህርት አካባቢዎችን ለማቅረብ ባለን ቁርጠኝነት ጸንተናል።ሁሉንም ተማሪዎች ለማስተማር ሕገ መንግሥታዊ ግዴታ አለብን።እርስዎ ከየትም ቢሆኑም፣ እዚህ ቦታ አልዎት።
በዲስትሪክታችን ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ አዳዲስ መመሪያዎችን እየተከታተልን ነው።አዳዲስ ትዕዛዞች ሲገቡ፣ የምንችለውን ያህል ግልጽነት ያለው እና የተረጋጋ መልእክት ለመስጠት እንሰራለን።
አንዳንድ ተማሪዎቻችን እና ቤተሰቦቻችን ወደ ትምህርታዊ ፍትህ በሚያደርጉት ጎዞ እና በነፃነት በመኖር ላይ ችግር እያጋጠማቸው ነው።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተከለሉት ቦታዎች እንዲወገዱ እና የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ አስከባሪ አካላት ተማሪዎችን ለማባረር ወደ ትምህርት ቤቶች ሊገቡ እንደሚችሉ የሚል የወጣው ማስታወቂያ ዲስትሪክታችን እና ማህበረሰቡን በእጅጉ እያሳሰበ ነው።
የትምህርት ዲስትሪክቶች የተማሪዎቹ ወይም የቤተሰቦቻቸው የኢሚግሬሽን ሁኔታ ምንም ይሁን ምን እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ነዋሪዎችን ያስተምራሉ።ለዚህም፣የስቴት ህግ የትምህርት ዲስትሪክቶች የኢሚግሬሽን ማስፈጸሚያዎችን ከፌደራል እና ከክልል ህግ ጋር በሚስማማ መልኩ በተቻለ መጠን እንዲገድቡ መመሪያ ይሰጣል።
ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች በዋሽንግተን ስቴት አቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሞዴል ፖሊሲ እና አሰራር መሰረት ዲስትሪክቱን ከፌደራል የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ጋር ያለውን ግንኙነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል አሰራር አለው።
በሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች፣እያንዳንዱ ተማሪ ደህንነቱ የተጠበቀ የትምህርት ቤት አከባቢ የማግኘት መብትን እናከብራለን።ትምህርት ቤቶቻችን የደህንነት እና የባለቤትነት ቦታዎች መሆናቸውን በድጋሚ እናረጋግጣለን።የተማሪዎቻችንን የደህንነት ስሜት ወይም ፍትሃዊ ትምህርት የማግኘት መብታቸውን የሚረብሽ ማንኛውንም እርምጃ አንታገስም።
በተጨማሪም፣non-binary ግለሰቦችን ጨምሮ የLGBTQIA+ ተማሪዎች እና ሰራተኞች መብቶች ለመጠበቅ ባለን ቁርጠኝነት ጸንተናል።ዲስትሪክቱ ሁሉን አቀፍ እና አጋዥ አካባቢን ለማሳደግ ባለው ቁርጠኝነት ጸንቷል።
የዲስትሪክቱ ዋና ሃላፊ አሰራር 3211 ዲስትሪክታችንን የተለያዩ ጽርዓተ-ፆታ ላላቸው ተማሪዎች የማይናወጥ ድጋፍ እንደሚያደርግ ይገልጻል።እያንዳንዱ ተማሪ የሚገባውን ሃብት፣ድጋፍ እና ክብር ማግኘት እንዲችል እነዚህን ልምዶች መጠቀማችንን እንቀጥላለን።
በአሁኑ ጊዜ እነዚህ ፖሊሲዎች ለተማሪዎች፣ለቤተሰቦቻቸው እና ለሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ሰራተኞች ግልጽ መረጃ ማቅረባቸውን ለማረጋገጥ ከህጋዊ ቡድናችን ጋር ተዛማጅነት ያላቸውን ፖሊሲዎች እና ሂደቶችን እየገመገምን ነው።
ተማሪዎቻችንን የሚጠብቁ ፖሊሲዎችን ለመደገፍ እና ለአካዳሚክ፣ማህበራዊ እና ስሜታዊ ደህንነታቸው ያለንን ቁርጠኝነት ለማጠናከር ከቤተሰቦች፣አስተማሪዎች እና የማህበረሰብ አጋሮች ጋር አብረን እንሰራለን።
ከትብብር ጋር፣
ዶክተር ብሬንት ጆንስ
ሱፐርኢንተንደንት
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች