Seattle Public Schools

የኮቪድ ወረርሽኝ ዝግጁነት

Summary : ለዛም ነው ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊ ከሆነ በትምህርት ቤቶቻችን ለሚከሰት የወረርሽኝ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን እንዲያውቁ የምንፈልገው።

ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ዝግጁ ነው:የኮቪድ ወረርሽኝ ዝግጁነት

የፀደይ ዕረፍት እየመጣ ነው፣እና ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የተማሪዎቻችን፣ሰራተኞቻችን እና ማህበረሰባችን ጤና እና ደህንነት ለማረጋገጥ ጠንክረን እየሰራን መሆኑን እንድታውቁ ይፈልጋል።

የኮቪድ-19 ጉዳዮች( COVID-19 cases)እና በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል መተኛት በማህበረሰባችን ውስጥ እየቀነሱ ስለመጡ፣በቅርብ ጊዜ የጤና ባለሥልጣናት የኮቪድ-19 መከላከያ መስፈርቶችን እንድንቀንሰ አስታውቋል። የኮቪድ-19 ጉዳዮች ማሽቆልቆል እና ክልከላዎች መቀነስ በአንዳንድ የኮቪድ መከላከያዎች ዘና እንድንል አስችሎናል በዚህም ትምህርት ቤቶቻችን ለተማሪዎች፣ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች የበለጠ ምቹ እንዲሆኑ አስችለዋል።

ሆኖም፣ወረርሽኙ ያላለቀ መሆኑን እንገነዘባለን፣እንዲሁም ተጨማሪ ለውጦች እና አዳዲስ ነገሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ እናውቃለን።ለዛም ነው ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች አስፈላጊ ከሆነ በትምህርት ቤቶቻችን ለሚከሰት የወረርሽኝ ጉዳይ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን እንዲያውቁ የምንፈልገው።

ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ለሚከተሉት በዝግጅት ላይ ነው

  • ሚያዝያ 18 ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳቸው በፊት በ24 ሰአታት ውስጥ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲያደርጉ  iHealth home rapid antigen tests home ለእያንዳንዱ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪ እና የስራ ባልደረባ መላክ
  • በመማርያ ክፍሎች፣ በትምህርት ቤቶች ወይም በማህበረሰቦች ውስጥ ለሚከሰቱ ጉዳዮች በፍጥነት ምላሽ እንድንሰጥ ቤተሰቦች በትምህርት ቤት የሚደረገውን በፍላጎት ላይ የተመሰረተ የኮቪድ-19 ምርመርራ( opt-in to in-school on-demand testing )እንዲያደርጉ እንዲመርጡ ማበረታታት -ተጨማሪ ዝርዝሮች በቅርቡ ይመጣሉ
  • አስፈላጊ ከሆነ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ማስኮች እና ፈጣን የኮቪድ መርመራዎች በትምህርት ቤቶች ማዘጋጀት።አሁን የቤት ውስጥ ምርመራ የበለጠ ተደራሽነት ስላለው፣ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ከመጋቢት 31 ጀምሮ በተወሰነ አጠቃቀም ምክንያት የክልል የምርመራ  ጣቢያዎቻችንን ይዘጋል።አስፈላጊ ከሆነ ድጋፉን እንደገና ለመክፈት ዝግጁ ነን።
  • እንደ ሲታመሙ ቤት መቆየት(staying home when sick)፣ምርመራ ማድረግ እና ጠንካራ የአየር  ዝውውር ያሉ የትምህርት ቤቶቻችን አስፈላጊ የኮቪድ የደህንነት እርምጃዎች መቀጠል።
  • የኮቪድ መጠን ሲጨምር፣እንደ ማስክ ማድረግ ያሉ የኮቪድ የደህንነት እርምጃዎችን መቼ ወደነበሩበት መመለስ እንዳለባቸው እቅድ ማውጣት

ቤተሰቦች ለሚከተሉት ሊዘጋጁ ይችላሉ

የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቻችን የሚማሩባቸው፣የሚያድጉባቸው እና የሚበለጽጉባቸው ቦታዎች ደህንነታቸው የተጠበቁ እና ጤናማ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለምታደርጉት ቀጣይነት ያለው እገዛ እናመሰግናለን። የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የኮቪድ መረጃ ለማግኘት ድህረ ገጻችንን ይጎብኙ (visit our website for SPS COVID information።) ጥያቄዎች ወይም ስጋቶች ካሉዎት፣እባክዎን እንነጋገርን( Let’s Talk)በመጠቀም ያነጋግሩን።