የ2021-22 መጨረሻ ዓመት የዋና ሃላፊ ጆንስ መልእክት
Summary : Gratitude and best wishes to you all for a safe and enjoyable summer.
የ2021-22 መጨረሻ ዓመት የዋና ሃላፊ ጆንስ መልእክት
ውድ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ፣
በዚህ ሳምንት በከተማው ውስጥ ባሉ የምረቃ ስነ ስርዓቶች ላይ ተመራቂዎችን ስናስመርቅ ለመላው የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ ምስጋና እና መልካም ምኞትን እልካለሁ።
ይህ ዓመት የተለየ ነው።ያልተጠበቁ ፈተናዎች ቢኖሩም ተማሪዎቻችን፣ቤተሰቦቻችን እና ሰራተኞቻችን መታየታቸውን ቀጥለዋል።እርስ በርሳችን መደጋገፍ በምንችልባቸው ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ልቤ ደስ ብሎታል።የዓመቱን መጨረሻ ማጠቃለያ ቪዲዮ ይመልከቱ።
የምንሰራው ስራ ለምን አስፈላጊ እንደሆነ በየቀኑ አስታውሳለሁ -ተማሪዎቻችን።አዳዲስ ፈጣሪዎች እንድንሆን እና ወደፊት ልቀት ላይ እንድናተኩር ያነሳሱናል።
ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ለፍትሃዊነት ያለው ቁርጠኝነት በአስፈላጊነቱ እና በአስቸኳይነቱ አድጓል። ስትራቴጂክ እቅዳችን፣Seattle Excellence፣የዘር እና የትምህርት ፍትሃዊነትን ያማከለ፣ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች እንደ ፀረ-ዘረኝነት ያሉ ስርዓት መልሶ በመገንባት ከትምህርት ፍትህ ርቀው የሚገኙ የቀለም ተማሪዎችን በተሻለ ሁኔታ ለማገለግል ያለመ ነው። ለተልዕኳችን ድጋፍ፣ድስትሪክቱ የተማሪን ውጤት ያተኮረ የአስተዳደር ሞዴል እያጠና ነው።በሚቀጥሉት ወራት ስለዚህ የአስተዳደር ሞዴል የበለጠ ይሰማሉ።
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ሰኞ፣ሰኔ 20፣ኦፊሴላዊ የJuneteenth በዓል ያከብራሉ።Juneteenth በ1865 Galveston, Texas በባርነት የቆዩት ነፃ መሆናቸውን የተረዱበት ቀን ነው።ዲስትሪክታችን የአፍሪካውያን አሜሪካዊያን የነፃነት ታሪካዊ ቅርስ ያከብራል።
በዚህ አመት በዲስትሪክታችን ዙሪያ መምህራን፣ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች እና አስተዳዳሪዎች የጀግንነት ስራ ሰርተዋል። ፈጠራ፣ትጋት እና ጽናት አሳይተዋል።ቤተሰቦቻችን ተማሪዎችን በመደገፍ እና በማገልገል ላይ እንደ አጋር ሆነዋል።የዚህ አመት ስኬቶች ያለ ሁላችሁም እገዛ አይሆኑም ነበር።የትምህርት አመቱ መጨረሻ ስኬቶችን የምናከብርበት ጊዜ ብቻ ሳይሆን ወደ አዲሱ ጉዞ የሚሸጋገሩትን አስተዋጾ እውቅና የምንሰጥበት ጊዜም ጭምር ነው።
ለተመራቂዎቻችን: እንኮራባችሃለን! በፊታችን ሁሉ ደስታ እና ብሩህ ተስፋ እመኛሎህ።የ 2022 ተመራቂ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላቹ!
ለሁላችሁም ምስጋና እና አስተማማኝ እና አስደሳች በጋ እንዲሆንላቸ መልካም ምኞቴ ነው።
ደህና ሁኑ፣
Dr. Brent Jones
ዋና ሃላፊ
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች