LGBTQ Pride
Posted on: June 1, 2025
Summary : ሰኔ 1 የLGBTQ + የኩራት ወር የመጀመሪያ ቀን ነው።
ሰኔ 1 የLGBTQ + የኩራት ወር የመጀመሪያ ቀን ነው።ዛሬ እና በየቀኑ የ LGBTQ+ ሰራተኞቻችን፣ተማሪዎቻችን እና ቤተሰቦቻችን እና ለሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦች የሚያበረክቱት አስተዋፅኦ እናከብራለን፡፡
ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተረጋገጠ የትምህርት እና የሥራ አካባቢዎችን ለመፍጠር ቁርጠኛ ነኝ፡፡እንደ የLGBTQ+ እና የ gender non-conforming ያሉ ሰዎች ያሏቸው ቦታዎች እያንዳንዳቸው እንክብካቤ እንደሚደረግላቸው፣ድምፃቸው እንደሚሰማ እና እገዛ እንደሚያገኙ ማወቅ ኣለባቸው።
ዛሬ ጠዋት በጆን እስታንፎርድ የትምህርት ልቀት ማዕከል (JSCEE) የኩራት እና የትራንስጀንደር ሰንደቅ ዓላማን ስንሰቅን ያለፈውን እና የአሁኑን ተጋድሎ፣ያሸነፉትን ድሎች እና ገና ያልተከናወኑ ስራዎች -ለመስራት ቃል የገባነውን ሥራ በአደባባይ እውቅና እየሰጠን ነው።
እኔ እንደ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ዋና ሃላፊ፣የ LGBTQ+ ተማሪዎቻችን፣ሰራተኞቻችን እና ቤተሰቦቻችን ሙሉ ማንነታቸው – በየቀኑ -እና በሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የበለፀጉ ሆነው በእውነት መታየት መቻላቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ ነኝ።
መልካም የኩራት ወር!
ከሰላምታ ጋር፣
ዋና ሃላፊ Brent Jones