Seattle Public Schools

ለሀገራዊ አደጋ ምላሽ

Summary : የእኛ ዋና ጉዳይ የተማሪዎቻችን ደህንነት ነው።

ውድ የሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች ቤተሰቦች፣

ባለፈው ማክሰኞ በ Uvalde, Texas, በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተፈጸመው አሰቃቂ የጅምላ ጥቃት( ቶኩስ) ዲስትሪክታችን እና ህዝባችንን በሀዘን ውስጥ ጥሎታል።

ከዚህ በኋላ፣ የድጋፍ መርጃዎችን እና በሁሉም ተማሪዎቻችን ደህንነት ያለንን ቁርጠኝነት ማጋራት እንፈልጋለን።

ተማሪዎች የዚህ አውዳሚ ክስተት ተጽእኖ ሳያድርባቸው አይቀርም።ስለ ጉዳዩ ከትምህርት ቤት፣ከመገናኛ ብዙኃን ወይም ከጓደኞቻቸው ሰምተው ይሆናል።ተማሪዎችዎ መረበሽ፣ፍርሃት፣ግራ መጋባት ወይም ቁጣ ሊሰማቸው ይችላል።

በቅርብ ጊዜ ስለተከሰቱ ክስተቶች አስመልክቶ ከልጅዎ/ልጆችዎ ጋር ለመወያየት እንዲረዳዎት መርጃዎች ከዚህ በታች አቅርበናል:

ክስተቱ የተከናወነው በትምህርት ቤት ስለሆነ፣ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻቸው ወይም በማህበረሰባቸው ውስጥ ስለ ደህንነታቸው ከፍተኛ ስጋት ሊሰማቸው ይችላል።የእኛ ዋና ጉዳይ የተማሪዎቻችን ደህንነት ነው።ትምህርት ቤቶች ደህንነታቸው የተጠበቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣እና ተማሪዎች እንክብካቤ እና ምቾት የሚያገኙበትን ቦታ ለማቅረብ ብዙ እርምጃዎችን እየወሰድን ነው።

ልባችን እና ሀሳባችን ከUvalde, ቤተሰቦች እና ማህበረሰብ ጋር ነው።በሚቀጥሉት ሳምንታት ከሚወዷቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ማሳለፍ እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ። ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ካሉዎት እባክዎን የእንነጋገር ቅጽ(Let’s Talk form) ይጠቀሙ።

ከሰላምታ ጋር፣
Dr. Brent Jones
Superintendent Seattle Public Schools