በ2022-23 የትምህርት ዓመት የትምህርት መጀመርያ ሰዓት የደረገ ለውጥ የለም
Summary : ትምህርት ቤት የመጀመሪያ ሰዓት ለመቀየር የቀረበው ሃሳብ አስመልክቶ ከብዙ ቤተሰቦች ስጋቶችን ሰምተናል።
የትምህርት ቤት የመጀመሪያ ሰዓት ለመቀየር የቀረበው ሃሳብ አስመልክቶ ከብዙ ቤተሰቦች ስጋቶችን ሰምተናል።
ዋና ሃላፊ ጆንስ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS)የ2022-23 የትምህርት ዓመት ትራንስፖርት ባለሁለት ደረጃ የትራንስፖርት ስርዓት( two-tier transportation system) እንዲቀጥል ወስኗል።ይህ ማለት የአንደኛ ደረጃ፣የK-8 እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች በመስከረም ላይ የትምህርት መጀመሪያ እና መጨረሻ ሰዓቶች አይለውጡም ማለት ነው።በአንዳንድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት መጀመርያ ሰዓት የ10 ደቂቃ ለውጥ ሊያዩ ይችላሉ።
ይህ ውሳኔ የትራንስፖርት አገልግሎትን ለማሻሻል መንገዶችን መፈለግ ስንቀጥል አሁን ያለውን መዋቅር እንድንቀጥል ያስችለናል።
ብሔራዊ የአውቶቡስ ሹፌር እጥረት፣ትራንስፖርት ለማግኘት ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በሙሉ ሙሉ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት አቅማችን ላይ ተጽእኖ ማሳደሩ ቀጥሏል። በ 2022-23 የትምህርት ዓመት ካለፈው መኸር ጀምሮ በነበረው ተመሳሳይ የተቀነሰ የአውቶቡስ አገልግሎት የምንጀምር ይሆናል።የተቋረጡትን የአውቶቡስ መንገዶች ወደነበሩበት መመለስ የምንችልበትን መንገድ ማጤን እንቀጥላለን።በስልታዊ እቅዳችን መሰረት፣ሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የቀለም ተማሪዎች እና ከትምህርታዊ ፍትህ ርቀው ያሉትን ተማሪዎች ለማገልገል ቅድሚያ ይሰጣል።
በሚቀጥሉት ወራት፣ያሉትን አስተማማኝ የትራንስፖርት አገልግሎት አማራጮች ማጥናታችንን ስንቀጥል የእርስዎን አስተያየት እና ግብአት ለማካፈል ብዙ እድሎች ይኖራሉ።ተማሪዎች በሰዓቱ ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ እና ለመማር ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን።
አስተያየቶችን ለሰጣቹ ቤተሰቦች በሙሉ እናመሰግናለን።ጥያቄዎች ወይም አስተያየቶች ካሉዎት እባክዎን በእንነጋገር ግብረመልስ ቅጽ(Let’s Talk feedback form)ላይ ያካፍሉን።እያንዳንዱን መልእክት እናነባለን እንዲሁም ግምት ውስጥ እናስገባለን።