የትምህርት የመጀመሪያ ሰዓት ለውጥ ፕሮፖዛል 2022-23
Summary : ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS) የቀጣዩ የትምህርት ዓመት የደወል ጊዜ (የትምህርት መጀመሪያ እና መጨረሻ ጊዜ) እንዲቀየር ሐሳብ አቅርቧል።
የትምህርት የመጀመሪያ ሰዓት ለውጥ ፕሮፖዛል 2022-23
ሲያትል የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (SPS) የቀጣዩ የትምህርት ዓመት የደወል ጊዜ (የትምህርት መጀመሪያ እና መጨረሻ ጊዜ) እንዲቀየር ሐሳብ አቅርቧል።ይህ አዲስ መርሃ ግብር የሚጀምረው በትምህርት የመጀመሪያ ቀን ነው።መስከረም 7 ለ ከ1ኛ -12ኛ ክፍል ተማሪዎች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ነው። መስከረም 12 የኪንደርጋርተን የመጀመሪያ የትምህርት ቀን ነው።
የትምህርት ቦርድ የሁሉም ትምህርት ቤቶች የደወል ሰዓትን ጨምሮ፣በ የ2022-23 የትራንስፖርት አገልግሎት ደረጃዎች ላይ በግንቦት ወር ድምጽ ይሰጣል።
የደወል ሰአቶችን መቀየር ማለት የቤተሰብ እና የሰራተኞች ፕሮግራም ማስተካከል ማለት እንደሚሆን እናውቃለን።
ለምን ተለወጠ?
በአሁኑ ጊዜ ሁለት የትምህርት መጀመርያ ሰዓቶች አሉ— አንዱ የአብዛኛዎቹ የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የትምህርት የመጀመሪያ ሰዓት ሲሆን ሁለተኛ ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች (ከ6-12 ኛ ክፍል) እና የK-8 ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች የትምህርት መጀመርያ ሰዓት ነው።ለውጡ የትምህርት መጀመርያ ሰዓት በሶስት ደረጃዎች ያስቀምጣል።
በዚህ የትምህርት ዓመት በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የአሽከርካሪዎች እጥረት ምክንያት ለመጓጓዣ ብቁ ለሆኑ ተማሪዎች አስተማማኝ የቢጫ አውቶቡስ አገልግሎት በመስጠት ረገድ ተግዳሮቶች ነበሩን።
በአሁኑ የትምህርት መጀመሪያ ሰአታት ለሚፈለጉ የትምህርት ቤት አውቶቡሶች በቂ አሽከርካሪዎች አልነበሩም።ይህ ማለት ዲስትሪክታችን አንዳንድ የአውቶቡስ መስመሮችን ማቆም ስለነበረበት በዚህ ምክንያት አንዳንድ አውቶቡሶች ከአንድ እስከ ሁለት ሰአት ዘግይተው ይደርሱ ነበር።
በአሁኑ ጊዜ በአሽከርካሪዎች እጥረት ምክንያት 50 የተቋረጡ የትምህርት ቤት የአውቶቡስ መስመሮች አሉ። በሀገር አቀፍ ደረጃ ያለው የትምህርት ቤት አውቶብስ አሽከርካሪዎች እጥረት በሚቀጥለው አመትም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
ወደ ሶስት-ደረጃ የትምህርት መጀመርያ ጊዜዎች ስርዓት(three-tier system) ስንቀይር እያንዳንዱ አሽከርካሪ ብዙ መስመሮችን እንዲሸፍን እና የሚፈለጉ የአሽከርካሪዎች ብዛት እንዲቀንስ ያስችላል። ይህ ዲስትሪክታችን ተከታታይ፣አስተማማኝ የተማሪዎች የመጓጓዣ ግብ እንዲያሳካ ያስችለዋል።
የ Three-Tier የጊዜ ሰሌዳ እንዴት ይሰራል?
ልክ እንደ አሁኑ እያንዳንዱ ትምህርት ቤት የትምህርት መጀመሪያ እና መጨረሻ ጊዜ ይመደብለታል። የእያንዳንዱ ትምህርት ቤት የትምህርት መጀመርያ እና መጨረሻ ሰአቶች ረቂቅ በዲስትሪክቱ ድረ-ገጽ ላይ ይገኛሉ።
እያንዳንዱ Tier ስንት ሰዓት ይጀምራል ?
አሁን ባለው ረቂቅ፣የሚከተሉትን የትምህርት የመጀመሪያ ጊዜዎች እያጤን ነው፡
- Tier 1: 7:30 a.m. ይጀምራል
- Tier 2: 8:30 a.m. ይጀምራል
- Tier 3: 9:30 a.m. ይጀምራል
አስተያየትዎ ወይም ጥያቄዎች
በእነዚህ ሶስት-ደረጃ የትምህርት መጀመርያ ሰዓቶች(three-tier system )እቅድ እንጀምራለን ብለን እንጠብቃለን።በዚህ ሽግግር ውስጥ ጥያቄዎች እና ፈተናዎች እንደሚኖሩ እናውቃለን።
እባክዎን እስካሁን ያላጤንናቸው ማናቸውንም ጥያቄዎች እና ተግዳሮቶች ለማስገባት ይህንን የ እንነጋገር አገናኝ(Let’s Talk link) ይጠቀሙ።
የጊዜ ቅደም ተከተል
የሶስት-ደረጃ የደወል ሰአቶች(three-tier bell times) በየ 2022-23 የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የትራንስፖርት አገልግሎት ደረጃዎች ውስጥ ይካተታሉ።
ሚያዝያ 21– ግንቦት 18: የትምህርት ቤት እና የማህበረሰብ አስተያየቶችን መሰብሰብ እና ማየት።
ሚያዝያ 21: የትምህርት ቤት ቦርድ ኦፕሬሽን ኮሚቴ — የተመከረውን ሀሳብ ይገመግማል እና ወደ ሙሉ የትምህርት ቤት ቦርድ ይላክ እንደሆነ ይወስናል።ወደ ቦርዱ ከመሄዱ በፊት በአስተያየቶቹ ላይ ለውጦች ሊደረጉ ይችላሉ።
ግንቦት 4: የትምህርት ቤት ቦርድ ስብሰባ — የመጓጓዣ አገልግሎት ደረጃዎች መነጋገር
ግንቦት 18: የትምህርት ቤት ቦርድ ስብሰባ — ቦርድ በየትራንስፖርት አገልግሎት ደረጃዎች ላይ ድምጽ ይሰጣል
በትምህርት ቤት መርሃ ግብሮች ላይ የሚደረጉ ማናቸውም ለውጦች ተግዳሮቶችን ሊያመጡ እንደሚችሉ እንረዳለን። ይህ ለውጥ ተማሪዎች በሰዓቱ ወደ ትምህርት ቤት መድረሳቸውን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።