ዳንድ ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ የትምህርት ቀን ዝማኔዎች
Posted on: April 26, 2025
Summary : በጥር 2022 ባጋጠመው የትምህርት ቀኖች መዘጋት ምክንያት በርካታ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የማካካሻ ቀናት ያስፈልጋቸዋል።
የአንዳንድ ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ የትምህርት ቀን ዝማኔዎች
በጥር 2022 ባጋጠመው የትምህርት ቀኖች መዘጋት ምክንያት በርካታ የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች የማካካሻ ቀናት ያስፈልጋቸዋል።
የእነዚህ ትምህርት ቤቶች የ2021-22 የትምህርት ዓመት መጨረሻ ቀን ከሌሎች ትምህርት ቤቶች በተወሰኑ ቀናት ይዘገያል።
ብዙ የሰራተኞች መቅረት ምክንያት፣ሰባት ትምህርት ቤቶች በጥር ወር ለተወሰኑ ቀናት ተዘግቷል።ተማሪዎች በአንድ የትምህርት ዓመት 180 ቀናት መማር አለባቸው የሚለው የስቴት ህግ ነው።የሕዝብ ትምህርት የበላይ ተቆጣጣሪ ጽሕፈት ቤት (Office of Superintendent of Public Instruction (OSPI)) ከሠራተኞች መቅረት ጋር የተገናኙ የትምህርት ቤቶች መዘጋት መካካስ እንዳለበት አሳስቧል። እነዚህ አስፈላጊ የማካካሻ ቀናት የእነዚህ ትምህርት ቤቶች የመጨረሻ የትምህርት ቀን ይለውጡታል።
ትምህርት ቤትዎ በዚህ ዝርዝር ውስጥ ከሌለ፣ የትምህርት ቤትዎ የትምህርት የመጨረሻው ቀን አርብ፣ሰኔ 17 ነው።
ማሳሰብያ: Juneteenth የሲያትል የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሰራተኞች በዓል ነው።ዘንድሮ ሰኞ፣ሰኔ 20 ይከበራል።
የመጨረሻው የትምህርት ቀን
- የ Cleveland ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጨረሻ የትምህርት ቀን ሐሙስ፣ሰኔ 23 ነው(3 የማካካሻ ቀናት ያስፈልጋሉ)
- የ Kimball አንደኛ ደረጃ ትምህርት የመጨረሻ የትምህርት ቀን ሐሙስ፣ሰኔ 23 ነው(3 የማካካሻ ቀናት ያስፈልጋሉ)
- የ Franklin ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጨረሻ የትምህርት ቀን እሮብ፣ሰኔ 22 ነው(2 የማካካሻ ቀናት ያስፈልጋሉ)
- የ Lincoln ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጨረሻ የትምህርት ቀን እሮብ፣ሰኔ 22 ነው(2 የማካካሻ ቀናት ያስፈልጋሉ)
- የChief Sealth ኢንተርናሽናል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጨረሻ የትምህርት ቀን ማክሰኞ፣ሰኔ 21 ነው(1 የማካካሻ ቀን ያስፈልጋል)
- የ Interagency የመጨረሻ የትምህርት ቀን ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 ነው(1 የማካካሻ ቀን ያስፈልጋል)
- የ Garfield ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጨረሻ የትምህርት ቀን ማክሰኞ፣ ሰኔ 21 ነው(1 የማካካሻ ቀን ያስፈልጋል)