Seattle Public Schools

Walk and Bike to School

Summary: ወደ ትምህርት ቤት በእግር እና ብስክሌት መሄድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ፣በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያለውን መጨናነቅ እና ብክለት ለመቀነስ እንዲሁም ማህበረሰብ ለመፍጠር አስደሳች መንገድ ነው።

Walk and Bike to School

ለምን ወደ ትምህርት ቤት በእግር እና ብስክሌት መሄድ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለማድረግ፣በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያለውን መጨናነቅ እና ብክለት ለመቀነስ እንዲሁም ማህበረሰብ ለመፍጠር አስደሳች መንገድ ነው።ወደ ትምህርት ቤት በእግር እና በብስክሌት የሚጓዙ ተማሪዎች የበለጠ ንቁ እና ለመማር ዝግጁ እንደሚሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ!

ምንድን የዲስትሪክቱ አሰተማማኝ የትምህርት ቤት መንገዶች አስተባባሪ (Sara Colling) (skcolling@seattleschools.org – 206-532-4453) በእነዚህ ሃሳቦች እና ሌሎችም ሊትረዳዎ ትችላለች ።

  • ወደ ትምህርት ቤት ብእግር ወይም በብስክሌት የሚሄዱ ቡድን ይምሩ። ተማሪዎች ተገናኝተው አብረው በእግር ወይም ብስክሌት መሄድ ይችላሉ።
  • በየትምህርት ቤት የእግር ጉዞ ቀን -ጥቅምት 12 ያግዙ።
  • እንደ የመንገድ ላይ የግድግዳ ሥዕሎች፣ሞቃታማ የክረምት ልብሶች እና የዝግጅት አቅርቦቶች ለመግዛት የሚያስችል እስከ $1,000 የሚያክል ገንዘብ ለማግኘት ለሲያትል የትራንስፖርት ድጎማ ዲፓርትመንት ያመልክቱ።
  • የስኬት ታሪኮች ያጋሩን እና በትምህርት ቤት እና በዲስትሪክት ጋዜጣዎች ላይ እናስተላልፋቸዋለን።